በክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የሚመራው የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን መከላከል ላይ አተኩሮ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ኮሚቴ ከተለያዩ የአለም ሀገራት ተሞክሮ ለመውሰድ የሚያስችለውን የቪዲዮ ኮንፍረንስ ዉይይት አካሂዷል።

በክብርት ሚኒስትር / ዳግማዊት ሞገስ የሚመራው የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን መከላከል ላይ አተኩሮ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ኮሚቴ ከተለያዩ የአለም ሀገራት ተሞክሮ ለመውሰድ የሚያስችለውን የቪዲዮ ኮንፍረንስ ዉይይት አካሂዷል።

**********

የቪዲዮ ኮንፍረንስ ዉይይቱ በዋናነት በትራንስፖርት ዘርፍ የቫይረሱን ስርጭት እንዴት መከላከል እንደሚቻል ትኩረት ያደረገ ሲሆን ለዉይይት መነሻ ሀሳብ ያቀረቡት የህክምና ባለሞያዎች የሆኑት / ፅዮን ፍሬዉ ከኒዉዮርክ እና አቶ ኖህ ኤሊያስ ከጄኔቭ እንዲሁም የትራንስፖርት ዘርፍ ባለሙያዎች የሆኑት ካሮሊኔ ሬይስ ከለንደን Global Resuluent Cities Network (GRCN) እና ኢማን አቡበከር World Resource Institute (WRI) ናቸው።

በሽታዉን ከመከላከል ረገድ የሀገራቸዉን ተሞክሮ በዝርዝር ያቀረቡ ሲሆን በገለፃቸዉም ስለ ኮሮና ቫይረስ የሌሎች አለምን ተሞክሮም ከትራንስፖርት ዘርፍ መደረግ ስላለበት ጥንቃቄ አብራርተዋል፡፡ በተለይም ማህበራዊ ፈቀቅታ የበሽታን ስርጭት ለመቀነስና አዳዲስ ህመምተኞች እንዳይኖሩ ለማድረግ ያለዉን ጠቀሜታ አስረድተዋል፡፡

ማንኛዉም ትራንስፖርት ስንጠቀም መስኮቶችን መክፍት ወይም ዉስጡን ቬንትተሌት ማድረግ፣ እንቅስቃሴዎችን በመገደብ በቤት መሆን ተመራጭ መሆኑን፣ እንዲሁም የእግር ጉዞ ወይም ብስክሌት በመጠቀም መመላለስ ቢለመድ በሚል በርካታ ጠቃሚ ምክሮችን ለግሰዋል፡፡ከተሳታፊዎች የተለያዩ ጥያቄዎች ተነስተዉ ምላሽና ማብራሪያ ከአቅራቢዎች ተሰጥቷል፡፡

በመጨራሻም ክብርት ሚኒስትር / ዳግማዊት ሞገስ ባለሙያዎቹን አመስግነዉ ከውይይቱ የተገኙትን እጅግ ጠቃሚ ተሞክሮዎች በሀገራችን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በሚደረገው ርብርብ ላይ ተግባራዊ ለማድረግ ያላቸውን ዝግጁነት አረጋጠው ለወደፊቱም ተመሳሳይ መድረኮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።