የዜና ክምችት የዜና ክምችት

Back

6ተኛው የሠንደቅ አላማ ቀን በትራንስፖርት ሚኒስቴር ተከበረ

 6ተኛው የሠንደቅ አላማ ቀን በትራንስፖርት ሚኒስቴር ተከበረ"ሰንደቅ ዓላማችን የብዘሃነታችን፣ አንድነታችንና የህዳሴያችን መገለጫ ነው" በሚል መሪ ቃል የዘንድሮው የሠንደቅ ዓላማ ቀን በትራንስፖርት ሚኒስቴር ተከብሯል፡፡ በወቅቱ የበዓሉ መልዕክቶች በአቶ ደረጀ ተፈራ የሚኒስቴር መ/ቤቱ ኰሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ቀርበዋል፡፡

የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሠራተኞች ለ6ተኛ ጊዜ "የድህነትና የኋላቀርነት ዘመን ከሀገራችን ተወግዶ ኢትዮጵያችን በልማትና፣ በዴሞክራሲ ጎዳና በፍጥነት ተራምዳ ሩቅ በማይባል ጊዜ ውስጥ መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ትሰለፍ ዘንድ የጀመርነውን የኢትዮጵያ ሕዳሴ ወደ ማይቀለበስ ደረጃ እናደርሳለን፡፡ በቀሩት ጊዜያትም የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዳችን ከመንግሥታችን ጎን ተሰልፈን ለማሳካት በሀገራችን ሰንደቅ ዓላማ ፊት ቃል እንገባልን" በሚል ቃለ መሃላ በማድረግ አክብረዋል፡፡

በዓሉ ሁሉም ሠራተኞች በተገኙበት በደመቀ መልኩ የተከበረ ሲሆን በዓሉን አስመልክቶ "የሰንደቅ ዓላማ እሴቶች' በሚል የግማሽ ቀን የፖናል ውይይት በሚኒስቴር መ/ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንደተካሄደ የኰሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ተፈራ ገልፀዋል፡፡