የዜና ክምችት የዜና ክምችት

Back

የሚኒስቴር መ/ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና ከመስከረም 28 እስከ 29/2006ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ በ2005 በጀት ዓመት አፈፃፀምና በ2006 ዓ.ም እቅድ ላይ ውይይት አድርገዋል፡

 የሚኒስቴር መ/ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና ከመስከረም 28 እስከ 29/2006ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ በ2005 በጀት ዓመት አፈፃፀምና በ2006 ዓ.ም እቅድ ላይ ውይይት አድርገዋል፡የሚኒስቴር መ/ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች ከመስከረም 28 እስከ 29/2006ዓ.ም በቢሾፍቱ ከተማ በ2005 በጀት ዓመት አፈፃፀምና በ2006 ዓ.ም እቅድ ላይ ውይይት አድርገዋል፡፡

የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒሰትር ክቡር አቶ ወርቅነህ ገበየሁ ውይይቱን ሲከፍቱ በ2005 ዓ.ም የስራ አፈፃፀም ላይ በጥልቀት በመወያየትና የነበረብንን ደካማና ጠንካራ ጎን በመለየት ከ2006 ዓ.ም ዕቅድ የተናጥልና የጋራ ሚናችን በመለየት የተቋማችን ተልዕኮና ራዕይ ማሳካት እንደሚገባ በውይይት ወቅት ገልፀዋል፡፡

በውይይቱ በ2005 በጀት አመት በሁሉን አቀፍ ገጠር መንገድ ተደራሽነት ፕሮግራምና በክልል መንገድ ግንባታ በስራ ዕድል ፈጠራ ጥሩ አፈፃፀም እንደነበርና በባቡር፣ በአየር ትራንስፖርት አገለግሎት፣ በመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት፣ በፖሊሲ ጥናትና በመንገድ ደህንነት ፖሊሲ ጥናት የነበሩ አፈፃፀሞችም ዋና ዋናዎቹን በስትራተጂክ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት ገለፃ ቀርቧል፡፡

በተሳታፊ ሰራተኞች ከመንገድ ግንባታ ጋር ተያይዞ የሚገነቡት መንገዶች ጥራት የመንገድ ትራፊክ አደጋ እያስከተለው ያለው ጉዳት የሚኒስቴር መ/ቤቱ ከተጠሪ ተቋማት ጋር ያለው ግንኙነትና ዘርፍ ከሚፈልገው የሰለጠነ የሰው ሀይል ጋር ተያይዞ የአቅም ግንባታ ስልጠና

ትኩረት ተሰጥቶ አልተሰራባቸውም የሚሉ ጥያቄዎችና ሐሳቦች ቀርበው ከሚመለከታቸው ሥራ ክፍሎችና የሚኒስቴር መ/ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡

በመጨረሻም ክቡር ሚኒስትሩ አቶ ወርቅነህ ገበየሁ በውይይቱ በተገኙ ግብዓቶች ትኩረት በመስጠት በሠራተኛውና በተቋሙ ያሉትን ችግሮች በመፍታት የተቋሙን የመሪነት ሚና በአግባቡ እንዲወጣ የበላይ አመራሩ ከፈፃሚው ጋር በመተጋገዝ በትጋት እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡