የዜና ክምችት የዜና ክምችት

Back

የአቶ መለስ ዜናዊ 1ኛ አመት መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ የትራንስፖርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ተካሄደ

 የአቶ መለስ ዜናዊ 1ኛ አመት መታሰቢያ ምክንያት በማድረግ የትራንስፖርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ተካሄደየትራንስፖርት ሚኒስቴር፣ የፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣንና የማሪታይም ጉዳዮች ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮችና ሠራተኞች የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስቴር አቶ መለስ ዜናዊን ለማሰብ "ራዕይህን ለማሳካት ቃላችንን እናድሳለን" በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላ አካሂደዋል፡፡

በመታሰቢያ ፕሮግራሙ የተገኙት የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ተክለፃዲቅ ሬባ በእለቱ ባደረጉት ንግግር ባለራዕዩ መሪ በሕይወት በነበሩበት ወቅት ከሀገራችን አልፈው ለመላው አፍሪካ የአረንጓዴ ልማት ኢኮኖሚ ተግባራዊ ለማድረግ ያደረጉትን ትግል በማሰብና ይህንኑ አጠናክሮ ለማስቀጠል የተካሔደ እንደሆነ ገልፀው ችግኝ መትከል ብቻ በራሱ ስኬት ስላልሆነ ከሱልልታ ከተማ አስተዳደር ጋር በመነጋገር ከእንሰሳትና ከሰው ንክኪ ነፃ አድርጎ በማጠር ሰራተኛውና አመራሩ ዕቅድ አውጥቶ እንደሚንከባከበውና ሚኒስቴር መ/ቤቱ በባቡር፣ በኤርፖርቶችና ከመንገድ ግንባታ ጋር ተያይዞ በሚደረጉ የትራንስፖርት መሠረተ ልማት ግንባታዎች ጎን ለጎን የአረንጓዴ ልማት ስትራተጂውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡

በሚኒስቴር መ/ቤቱ የኰሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ደረጀ ተፈራ የጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ አንደኛ አመት ለመዘከር እና ይህንኑ ምክንያት በማድረግ የተደረገው ችግኝ ተከላ በአንድ ግዜ የሚቆም ሳይሆን የአረንጓዴ ልማት ንቅናቄው ጎልብቶ በህዝቦች የጋራ ትብብር በሀገራችን ለውጥ እስኪመጣ ድረስ ጥረቱ መቀጠል እንዳለበት እና ሠራተኞችም የክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴሩን ራእይ ለማሳካት ዳግም ቃላቸውን ያደሱበት እንደሆነ ገልፀዋል፡፡