የዜና ክምችት የዜና ክምችት

Back

የትራንስፖርት አከናዋኝ የንግድ ስራ ፈቃድ ለመስጠት እና ብቃትን ለማረጋገጥ በተዘጋጀ ረቂቅ መመሪያ ላይ ከአጋር አካላት ጋር ውይይት ተደረገ፡፡

የትራንስፖርት አከናዋኝ የንግድ ስራ ፈቃድ ለመስጠት እና ብቃትን ለማረጋገጥ በተዘጋጀ ረቂቅ መመሪያ ላይ ከአጋር አካላት ጋር ውይይት ተደረገ፡፡
*****
የኢ.ፌ.ድ.ሪ. ትራንስፖርት ሚኒስቴር የሃገሪቱን የሎጀስቲክስ ስርዓት በዘመናዊ ቴክኖሎጅ የታገዘ በማድረግ የሃገሪቱን የወጪ እና ገቢ ንግድ ለማሳለጥ የትረንስፖርት አከናዋኝ የንግድ ስራ ለመስጠት እና ብቃትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ረቂቅ መመሪያ በማዘጋጀት እና ዘርፉ የሚመለከታቸውን አጋር አካላት እና ተጠሪ ተቋማትን ባሳተፈ መልኩ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡
የማሪታይም ጉዳዮች ባለስልጣን ስለ መመሪያው አስፈላጊነት ሲያብራሩ ሃገራዊ ሪፎርሙን መሰረት ያደረገና የግል ባለሃብቶችን ለማሳደግ የሚረዳ፣ በውድድር ላይ የተመሰረተ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል፣ የሎጂሰቲክስን ገቢና ወጪ ለመቀነስ የሚያግዝ እና የመልቲ ሞዳል ሰንሰለት አገልግሎትን ተደራሽ ለማደረገ የሚያስችል እንደሆነ አብራርቷል፡፡
በውይይቱ የተራንስፖርት ሚኒስቴር፤ የማሪታይም ጉዳዮች ባለስልጣንና በሎጅሰቲከሰ ዘርፍ የተሰማሩ የግል ባለሃብቶች የተገኙ ሲሆን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ መመሪያው ከመጽደቁ በፊት ተደጋጋሚ ውይይት ማደረጉን አመሰግነው በረቂቅ መመሪያው የተቀመጠው ካፒታል የተጋነነ እና ሊሻሻል የሚገባው እነደሆነ፡ የአገልግሎት ሰጭዎቸ ቁጥር በአምስት መወሰኑ ብዙሃኑን እንደማያሳትፍ እና የሚጠይቀው የስራ ልምድ የተጋነነ በመሆኑ ቢሻሻሉ የሚሉ አሰተያቶች ተነስተው ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡