የዜና ክምችት የዜና ክምችት

Back

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ለገና በዓል ያስተላለፉት መልእክት

የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ለገና በዓል ያስተላለፉት መልእክት

ለመላው ኢትዮጲያውያን የክርስትና እምነት ተከታዩች በሙሉ መልካም የገና በዓል እንዲሆንላችሁ እየተመኘሁ በዓሉን ስናከብር እራሳችንንና ቤተሰቦቻችንን ከአስከፊውና ከአሰቃቂው የመንገድ ላይ ትራፊክ አደጋ እንጠብቅ!

እንደሚታወቀው በበዓላት ወቅት ጠጥቶ ማሽከርከር ለመንገድ ትራፊክ አደጋ መከሰት በዋነኛነት የሚጠቀስ በመሆኑ አሽከርካሪዎች በዓሉን ሲያከብሩ በከፍተኛ የኃላፊነት መንፈስ እንዲያሽከረክሩ ላሳስብ እወዳለሁ፡፡

ስለሆነም አሽከርካሪዎችና እግረኞች አስፈላጊውን ጥንቃቄ በማድረግ እራሳችሁንና ቤተሰቦቻችሁን ከመንገድ ትራፊክ አደጋ እንድትጠብቁ እጠይቃለሁ፡፡

መልካም የገና በዓል!!