የዜና ክምችት የዜና ክምችት

Back

በዓይነቱ ልዩ የሆነው የአዲስ አበባ አዳማ የፍጥነት መንገድ ተመረቀ

በዓይነቱ ልዩ የሆነው የአዲስ አበባ አዳማ የፍጥነት መንገድ ተመረቀመንገዱ 80.4 ኪ ሜትር ርዝመት ሲኖረው በአንድ ጊዜ ትይዩ ስድስት መኪናዎችን ማስተናገድ የሚችል እና የክፍያ ጣቢያዎች ያሉት ነው፡፡
ከዚህ በፊት ከአዲስ አበባ አዳማ ለመድረስ ከሁለት ስዓት እስከ ሦስት ስዓት የሚፈጅ ሲሆን ይህ መንገድ በመገንባቱ ወደ 45 ደቂቃ ዝቅ አድረጎታል:: የኢፌደሪ ጠ/ሚኒስተር አቶ ኀ/ማሪያም ደሳለኝ የመንገዱ መገንባት የኢኮኖሚያዊ እድገቱ ወሳኝ ነው ያሉ ሲሆን ኢትዮጵያ በጂቡቲ በኩል ለምታደርገው ለገቢና ወጪ ንግድ ለማቀላጠፍ ወሳኝ ነው ያሉት አቶ ኀ/ማርያም ደሳለኝ የመንገድ መግንባታ በቀጣይ እሰከ ጅቡቲ ይደርሳል ብለዋል::

የቻይናው ጠ/ ሚኒስተር ሊ ከ ቺያንግ በበኩላቸው በአዲስ አበባ በአደረጉት ጉብኝት ኢትዮጵያ በተለያዩ ቦታዎች የመሰረተ ልማት ግንባታዎች እያካሄደች መሆኑ እና እድገተም በጥሩ ሁኔታ ላይ አንደሚገኝ ተናግረዋል:: የመንገድ መገንባት የቻይና እና የኢትዮጵያን በማህበራዊ በፖለቲካዊ እና በኢኮኖሚያዊ ዘርፍ ያላቸውን ትስስር ያሳያል ብለዋል::
በቻይናናበኢትዮጵያ የጋራ ትብብር በ11 ቢሊዮን ብር የተገነባው የፍጥነት መንገድ በግንባታው ወቅት 90% በላይ ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎችን ያሳተፈ ሲሆን መንገዱ ስራ ላይ ሲጅምር ለ400 በላይ ሰዎች የስራ ዕድል እንደሚፈጠር ተገልፇል፡፡