የዜና ክምችት የዜና ክምችት

Back

የአዲስ አዳማ የፍጥነት መንገድ የደህንነት አስተዳደር

የአዲስ አዳማ የፍጥነት መንገድ የደህንነት አስተዳደር ሥራው ትኩረት ተሰጥቶ በመስራቱ ለውጦች መመዝገብ መጀመራቸውን ኢትዮጵያ የክፍያ መንገድ ኢንተርፕራይዝ አስታወቀ፡፡

የኢንተርፕራይዙ ዋና ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ሕይወት ሞሲሳ ለጋዜጠኞች መግለጫ በሰጡበት ወቅት እንደተናገሩት፤ መንገዱ አገልግሎት መስጠት ከጀመረ አንስቶ በየወሩ የአንድ አሊያም የሁለት ሰው ሕይወት እየጠፋ ነው፡፡

በተያዘው ዓመት ከመስከረም ወር እስካለፈው የካቲት ወር ድረስ ብቻ ወደ 73 አደጋዎች የተመዘገቡ ሲሆን፤ አደጋውን ለማስወገድ የደህንነት ሥራው ላይ ተጨማሪ ሥራ መስራት እንዳለበት ታውቋል፡፡ የደህንነት አስተዳደር ሥራው በመጠናከሩ ባለፈው ወር ለውጥ መታየት ጀምሯል፡፡