የዜና ክምችት የዜና ክምችት

Back

በምእራብ ሸዋ -አምቦ ና ምስራቅ ወለጋ -ነቀምቴ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥና የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ያለበት ደረጃ አጥጋቢ ነው ተባለ

 በምእራብ ሸዋ -አምቦ ና ምስራቅ ወለጋ -ነቀምቴ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥና የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ያለበት ደረጃ አጥጋቢ ነው ተባለበመንገድ ትራፊክ ደህንነት  በአምቦ እና  በነቀምቴ ያለው እንቅስቃሴ  ለሌሎች አካባቢዎች   እንደተሞክሮ ሊወሰድ እንደሚገባው የትራንስፖርት ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

በምእራብ ሸዋ  አምቦ ከተማ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት እንቅስቃሴን ሲታይ እግረኞች ግራቸውን ጠብቀው በመጓዛቸው የአደጋ መንስኤ የሆኑ ምክንያቶች እቀነሱ መምጣታቸው በየትምህርት ቤቱ ስለ መንገድ ደህንነት ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኮች በተማሪ ትራፊክ ክለብ አማካኝነት መሰጠቱ የአካባቢው ህብረተሰብ ስለ መንገድ አጠቃቀም ያለው ግንዛቤ ከፍ እያለ ምምጣቱ እንዲሁም የትምህርቱ ስርፀቱ እያደገ መምጣቱ  እየተከናወኑ ያሉ አበይት ተግባራት ናቸው፡፡

በምእራብ ኦሮሚያ ነቀምቴ ከተማ ደግሞ ህብረተሰቡ ከትራፊክ አደጋ ራሱን እንዲጠብቅና ለአሽከርካሪዎች ስለ መንገድ ትራፊክ ደህንነት የታሀድሶ ትምህርት መሰጠቱ በነቀምቴ ከተማ የትራፊክ ምልክቶችና ዜብራ ለመስራት ጥረት እተደረገ መሆኑ ተጠቃሽ ነው፡፡

በህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ረገድ ህብረተሰቡ በፈለገው ደረጃ የትራንስፖርት አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል፡፡ በተለይም ከአምቦ አዲስ አበባ በመናሃሪያ ውስጥ ተጓዦች በፈለጉበት ሰዓት እንዲስተናገዱ የተደረገበት ስርዓት እንዳለ ነው፡፡ ተሸከርካሪዎች በየደረጃቸው በሚገለገሉበት ታሪፍ መሰረት የውድድር መንፈስ በማዳበር እንዲሰሩ እየተደረገ ነው፡፡ ትርፍ መጫንና ትርፍ ማስከፈልን በተመለከተ አምቦና በአምቦ ዙሪያ ያሉ ወረዳዎች ቁጥጥር የሚያደርጉበት ሂደት እንደለ ታውቋል፡፡

    

የምስራቅ ወለጋ ነቀምቴ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ ረገድ በትራንስፖርት አገልግሎት አሠጣጡ የሚታየውን የፍላጎትን አቅርቦት አለመመጣጠን ለመፍታት ግብረ ሃይል በማቋቋም መፍታት ተችለዋል፡፡ ከክምችት ጊዜ በስተቀር በመናሃሪያ ውስጥ ተጓዥ ከ40ደቂቃ በላይ አይቆይም ፡፡

የትራንስፖርት ሚኒስቴር በጥራትና በዋጋ ትራንስፖርቱ ተደራሽ መሆን መቻል አለበት ብሎ ያምናል፡፡ በመሆኑም በትራንስፖርት መሰረተ ልማት ግንባታን አገልግሎት አሰጣጥ ህብረተሰቡ ተጠቃሚ ለማድረግ የትራንስፖርት ሚኒስቴር እየሰራ ይገኛል፡፡ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የጀመራቸውን መልካም ተሞክሮዋች አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በምእራብ ሸዋ-አምቦ  ያለው የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ተሞክሮ  ተጠቃሽ የሆነው የአምቦ ከተማ ሊበረታታ ይገባዋል፡፡ የመንገድ ትራፊክ አደጋ ኢኮኖሚዊ ተፅዕኖ በሃገር እንዲሁም በንብርትና ህይወት ላይ ውድመትን ያስከትላል፡፡ ህብረተሰቡን ስለ መንገድ ደህንነት በማስገንዘብ በመረጃው ተደራሽ ማድረግ መቻል አለብን በማለት ይገልፃል፡፡