News News

ከ600 ሚልዮን ብር በላይ የተገዙ የተለያዩ ለመንገድ ጥገና የሚውሉ ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎች ለክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ተበረከተ።

የትራንስፖርት ሚኒስቴር ከመንገድ ፍንድ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ባዘጋጀው ለክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ድጋፍ የተገዙና ለመንገድ ጥገና የሚውሉ የተለያዩ ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎች የርክብክብ ሥነሥርዓት ላይ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ አደም ፋራህ ፣ ክብርት ሚንስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ፣ ክቡራን የሚንስትር ዴኤታዎች፣ የክልል እና የከተማ አሰትዳደር ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች፣ የተጠሪ ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል። የኢፌዴሪ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ በዕለቱ ባስተላለፉት መልዕክት ለመንገድ ግንባታ የምንሰጠው ያክል ትኩረት ለመንገዶች እንክብካቤም ማድረግ አለብን ያሉ ሲሆን ከመንገድ ጥገና ጋር ተያይዞ የሚታዩ ችግሮችን ከመፍታት አንጻር ትልቅ ሚና የሚኖረው የክልል እና የከተማ አስተዳደር የመንገድ ኤጀንሲዎች አቅም ለመገንባት በትራንስፖርት ዘርፍ 10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ በተያዘው መሠረት የተለያዩ ማሽነሪዎችና ተሽከርካሪዎች ማስረከብ በመቻሉ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዘርፍን ማቀላጠፍ ለብሔራዊ ልማትና ኢኮኖሚያዊ እድገት አስፈላጊ መሆኑን ገለጹ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዘርፍን ማቀላጠፍ ለብሔራዊ ልማትና ኢኮኖሚያዊ እድገት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል:: “የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዘርፋችንን ማቀላጠፍ ለብሔራዊ ልማትና ኢኮኖሚያዊ እድገት አስፈላጊ መሆኑን እንገነዘባለን፤ ለዚህም ነው በዚህ ዙሪያ የኢትዮጵያብልጽግናራዕይ ትኩረት እያደረግን ያለነው” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ:: የኢትዮጵያ ብልጽግና ራዕይን ትኩረት በመድረግ በትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ዘርፍ የባለፉት ሦስት ዓመታት አብይት ክንውኖችን ገልጸዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ አገር አቀፍ የትራንስፖርት ፖሊሲ፤ አገር አቀፍ ሎጂስቲክስ ፖሊስ፤ ብሄራዊ ሎጂስቲክስ ስትራቴጂ እና ሞተር-አልባ የትራንስፖርት ስትራቴጂዎች መነደፋቸውን ገልጸዋል፡፡

በኮቪድ-19 መከላከል ላይ የሚታዩ መዘናጋቶች ታርመው በልዩ ትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ተጠቆመ፡፡

የትራንስፖርት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር የኮቪድ-19 አደጋን መከላከል ላይ ያለፈውን የ9 ወራት አፍጻጸም በዝርዝር ገምግሟል፡፡ በግምገማውም በሚኒስቴር መ/ቤቱና በ10ሩም ተጠሪ ተቋማት በጥንካሬ እየተሰሩ ያሉ የመከላከል ስራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉና በተለይም መዘናጋት በሚታይባቸው ተቋማትና የብዙሃን ትራንስፖርት አገልግሎት በሚሰጥባቸው ቦታዎች የሚታዩ ክፍተቶች በፍጥነት እንዲታረሙ በግምገማው ወቅት በዝርዝር ተነስቷል።

#ኢትዮጵያንእናልብሳት #GreenLegacy

አገራችን እየተፈተነችበት ያለውን የጎርፍ መጥለቅለቅ፣ የምግብ ዋስትናን በአስተማማኝ ሁኔታ ያለማረጋገጥና አካባቢ ተኮር ግጭቶች የመከላከያ መንገዱ በሁሉም ኢትዮጵያዊ እጅ ላይ ነው፡፡ ኑ! ሁላችንም በአንድነት “ኢትዮጵያን እናልብሳት”

የትራንስፖርት ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማቱ ዘርፉን የማዘመን ጥረት የሚበረታታ መሆኑ ተገለጸ።

የትራንስፖርት ሚኒስቴርና የተጠሪ ተቋማቱ ዘርፉን የማዘመን ጥረት የሚበረታታ መሆኑ ተገለጸ። የትራንስፖርት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማቱ ዘርፉን ለማዘመን እያደረጉት ያለው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስታወቀ። የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ አሸናፊ ጋዕሚ ሚኒስቴሩና ተጠሪ ተቋማቱ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ዘርፉ የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ የሔዱባቸው ርቀቶች ውጤታማ ናቸው ብለዋል። በመንገድ ግንባታና ጥገና፣ በማሪታይምና ሎጂስቲክስ፣ በመንገድ ፈንድ ገቢ አሰባሰብና በሌሎችም መስኮች ሁሉን አቀፍና አሳታፊ ተግባራት መከወናቸው ለአፈፃፀሙ ውጤታማነት አስተዋጽኦ ማድረጉን ጠቅሰዋል። በዋናነትም ለበርካታ ዓመታት ጥያቄ ሲያስነሳ የቆየው የትራንስፖርት ፖሊሲ መጽደቁና ስራ ላይ መዋሉ እቅዱ እንዲሳካ ማገዙን ተናግረዋል። ከመንገድ ግንባታ ጋር ተያይዞ ውስብስብ ችግር መኖሩ ይታወቃል ያሉት ሰብሳቢው ይህም ሆኖ ያለፉት ዘጠኝ ወራት የፕሮጀክቶች አፈፃፀም 80 በመቶ መድረሱ ትልቅ ውጤት እንደሆነ ገልጸዋል። የወጪ ገቢ እቃን በማሳለጥ ፍጥነት እንዲኖር በማድረግ ረገድም የሚቆጠሩ ተግባራት መከናወናቸውን በተለይ የወደብ ቆይታን አስመልክቶ የነበሩ ማነቆዎች የመፈታት ሁኔታም መሻሻሉን ጠቅሰዋል። የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ዳግማዊት ሞገስ ዘርፉ ለተለያዩ መስኮች አስቻይ የሆነ መሰረት የሚጣልበት በመሆኑ ከፍያለ ትኩረት እንደተሰጠው ተናግረዋል። ሚኒስትሯ የሕዝቡን የመንገድ መሰረተ ልማት ፍላጎት መነሻ በማድረግና በዋናነት የግብርና፣ የማኑፋክቸሪንግና ኢንዱስትሪ፣ የማዕድንና የቱሪዝም መስኮችን እንዲደግፍ እየተሰራ ነውም ብለዋል።

የታወቁ አገልግሎቶች የታወቁ አገልግሎቶች

Back

የትራንስፖርት ሚኒስቴር - የ10 መሪ የልማት ዕቅድ

Download Resource

Video/ቪድዮ Video/ቪድዮ