በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር “ከጳጉሜን እስከ ጳጉሜን #እንደርሳለን!” የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ንቅናቄ ጳጉሜን 3 #የቁጥጥር ቀን ሆኖ ተከብሮ መዋሉ ተገለፀ።

በባለስልጣን መስሪቤቱ ድሬደዋ ቅርኛጫፍ ጽ/ቤት ዋና ዳሬክተር ወ/ሮ ሰአዳ አዋሌ እንደተናገሩት ዜጎቻችንን በየለቱ እየቀጠፈ የሚገኘውን የትራፊክ አደጋ ለመከላከል የሁሉም ባለድርሻ አካላት ቅንጅታዊ ርብርብ ወሳንነት አለው ብለዋል ፡፡ ለዚህም ባለስልጣን መስሪያቤቱ ከመድረኩ የሚነሱ ግብአቶቸን በመጠቀም በአዲሱ አመት በተቀናጀና በተደራጀ መልኩ እየደረሰ ያለውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ ይሰራልም ነው ያሉት፡፡
በመድረኩ ተሳታፊ የሆኑ አካላትም የመንገድላይ የትራፊክ አደጋን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ሚጠበቅባቸውን ለመወጣትና ጠቀናጅቶ ለመስራት መዘጋጀታቸውን ገልፀው ጽ/ቤቱም በቀጣይ መሰል የምክክር መድረኮችን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡
በቀጣይ ጳግሜ 3 የመንገድ ላይ ቁጥጥር መርሀግብር የተካሄደ ሲሆን በዚህም ከህጉ ውጥ በሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎችን የመቆጣጠር ስራ ተከናውኗል፡፡ በዚህ የቁጥጥር ስራም የቅርንጫፍ ጸ/ቤቱ ዋና ዳይሬክተር የአስተዳደሩ ትራፊክ ጽ/ቤት ሀላፊን ጨምሮ የመንገድ ደህንነት ተቆጣጣሪዎችና የትራፊክ ፖሊሶች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የዜና ክምችት የዜና ክምችት