በሶማሌ ክልል ደወሌ ላይ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል የተጀመረዉ የድንበር ተሻጋሪ የጭነት ተሸከርካሪዎች ተርሚናል ግንባታ በጥሩ አፈጻጸም ላይ መሆኑ ተገለጸ፡፡

የኢፌዴሪ ትራንሰፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ሙሉ ገ/እግዚአብሐር የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የሚረዳ የድንበር ተሻጋሪ የጭነት ተሸከርካሪዎች ተርሚናል ግንባታ ሂደትን በአካል የጎበኙ ሲሆን የአፈጻጸም ደረጃዉም በዕቅዱ መሠረት መሆኑን ለማየት ችለዋል።
በሶማሌ ክልል በግሊሌ ሲቲ ዞን አይሻ ወረዳ ደወሌ ቀበሌ ላይ እየተገነባዉ የሚገኘዉ የድንበር ተሻጋሪ የጭነት ተሸከርካሪዎች ተርሚናል የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል የሚያግዝ ከመሆኑም በላይ ለመኪኖች ማቆያና ለሹፌሮች የሚሆን የተለይዩ አገልግሎቶችን የሚሰጥ መሆኑ ታወቋል።
በቅርቡ የኢፌዴሪ ትራንሰፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ለደወሌ ተርሚናል ግንባታ ስኬት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ተገቢውን የድጋፍ፣ የክትትልና የቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋት ለግንባታው በስኬት መጠናቀቅ አስፈላጊውን ትብብር እንደሚያደርጉ ቃል መግባታቸዉ ይታወሳዋል።

የዜና ክምችት የዜና ክምችት