‹‹የኮቪድ-19 ወረርሽኝና የሎጂስትክስ ዘርፍ›› በሚል ርዕስ 14 ኛው ዙር ዌብናር ተካሄደ

አለም አቀፍ ልምድ የሚቀርብበት ሳምንታዊው የዌብናር ውይይት ለ14 ኛ ግዜ ‹‹ የኮቪድ-19 ወረርሽኝና የሎጂስትክስ ዘርፍ›› በሚል ርዕስ የተካሄደ ሲሆን ውይይቱን ተከትሎ በኢፌዴሪ ትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር በክብርት ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ ማጠቃለያና የቀጣይ አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
አለም አቀፉ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ በሎጂስትክስ አገልግሎቱ ላይ ሚያሳድረውን ጫና ለመቀነስና ወረርሽኙን ለመከላከል የሚያስችል አለም አቀፍ ተሞክሮ በቀረበበት የውይይት መድረክ ላይ ውይይቱን በንግግር የከፈቱት በትራንስፖርት ሚኒስቴር የሎጂስትክስና የባቡር ዘርፍን የሚከታተሉት ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር አቶ አወል ወግሪስ ሳምንታዊው የውይይት መድረክ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ለሚያከናውናቸው ዘርፈ ቡዙ ስራዎች መሳካት የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሆነ ገልፀው በ14ኛው ዙር የዌብናር ውይይት በሎጂስትክስ ዘርፍ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የሚያስከትለውን ጫና ለመቀነስ ከአገራት የሚገኘው ልምድ ከነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም መተግበር እንደሚያስፈልግ ጠቅሰዋል፡፡
በውይይቱ ላይ ፕሮፌሰር ግርማ ገ/ሰንበት፣ ዶ/ር ተጫኔ ቦሰአና እና ኢንጂነር አቤል ከበደ ከስውዲሽ ዩኒቨርስቲ እንዲሁም ከኔዘርላንድ ኢንጂነር ሪኢድ አሊመሃመድን ጨምሮ በዘርፉ ምርምር የሚያካሂዱ ሙሁራን ለውይይት መነሻ ፁሁፍ አቅርበው በተሳታፊዎች ውይይት ተደረጎበታል፡፡

የዜና ክምችት የዜና ክምችት