ጥቅምት 1 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 12፡00 ጀምሮ የብስክሌት እና የእግረኞች ቀን መርሃ ግብር በየአካባቢው የእግር ጉዞዎች እና የብስክሌት እንቅስቃሴዎችን በማካሄድ የሞተር አልባ ትራንስፖርት የማበረታታት ፕሮግራም ይካሄዳል፡፡

በሀገራችን የትራፊክ አደጋ የሰውን ህይወት ከመቅጠፍና አካልን ከማጉደሉ ባሻገር በንብረት ላይ እያስከተለ ያለውን ተፅዕኖ ለመቀነስ የትራንስፖርት ሚኒስቴር የህብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ የሚያስችል "ከጷጉሜን እስከ ጷጉሜን እንደርሳለን" በሚል መሪ ሀሳብ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ንቅናቄ ፕሮግራሞችን በተለያዩ ስልቶች እና የኮሙኒኬሽን አግባቦች በመጠቀም በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
ስለሆነም ጥቅምት 1 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 12፡00 ጀምሮ የብስክሌት እና የእግረኞች ቀን መርሃ ግብር በየአካባቢው የእግር ጉዞዎች እና የብስክሌት እንቅስቃሴዎችን በማካሄድ የሞተር አልባ ትራንስፖርት የማበረታታት ፕሮግራም ይካሄዳል፡፡
መርሃ ግብሩን በማስመልከት የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ መልእክት አስተላልፈዋል ፡፡
ክብርት ሚኒስትሯ:-
‹‹ጥቅምት 1 በሚከናወነው ሀገር አቀፍ #የብስክሌተኞች እና #የእግረኞች ቀን በአካባቢያችን በመሳተፍ ለትራፊክ አደጋ የማይጋለጥ የመንገድ ላይ እንቅስቃሴ በሀገራችን እንዲኖር እና አደጋው እንዲቀንስ የበኩላችንን ሚና እንወጣ!›› የሚል መልእክት አስተላልፈዋል፡፡

የዜና ክምችት የዜና ክምችት