የትራንስፖርት ዘርፉን በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ማዘመን ልዩ ትኩረት ተሰጥቶበታል።

የትራንስፖርት ዘርፉን በዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ማዘመን ልዩ ትኩረት ተሰጥቶበታል።
**********************
ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ በፓናል ዉይይቱ ተሳታፊዎች ለተነሳዉ ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ እንደተናገሩት የትራንስፖርት ዘርፉን ተወዳዳሪ ለማድረግና የግሉን ዘርፍ በስፋት ለማሳተፍ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በስፋት በዘርፉ መጠቀም ልዩ ትኩረትእንደተሰጠዉ ገልጸዉ የኮቪድ-19 ስርጭትን ለመከላከል በፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ከሚሰጡ አገልግሎቶች ከ26 በላይ አገልግሎቶችን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ መሰጠት መጀመሩን አብራርተዋል።
በሁለት ዙር በተደረገዉ የፓነል ዉይይት በገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ አወያይነት በትራንስፖርት ዘርፍ ለግሉ ባሀብት የተመቻቹ ዕድሎች ላይ እንዲሁም በገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ያስሚን ዎሃብreቢ አወያይነት በትራንስፖርት ዘርፍ ለዓለም አቀፍ ተቋማትና ለውጪ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት የተመቻቹ መልካም ዕድሎች ላይ ፓናል ዉይይት ተደርጓል።
በዉይይቱም ዘርፉ በጣም ዉስብስብና ሰፊ ከመሆኑም በላይ ትልቅ ቅንጅታዊ ሥራን የሚጠይቅ ነዉ ብለዋል። የተለያዩ ፖሊሲዎችና ስትራቴጅዎች ጸድቀዉ መተግበራቸዉና ለግሉ ባለሀብት የተመቻቸ መደላድሎች መፈጠራቸዉ የብዙሃን ትራንስፖርት ላይ ትኩረት መደረጉ፣ የሞተር አልባ የትራንስፖርት ስትራቴጅ መተግበሩን በበጎ ሁኔታ ያቀረቡ ሲሆን የተጀመረዉ የአሰራርና አደረጃጀት እንዲሁም የሰዉን አቅም የመገንባት ሥራ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አሳስበዋል።
3 ትሪሊዮን ብር የሚጠይቀዉ የትራንስፖርት ዘርፍ የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድን ለማሳካት በተለይም ለዘርፉ የተዘጋጁ የፋይናንስ ድጋፍ ዕድሎች ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራና ተመሳሳይ መድረኮችም በቀጣይነት መኖር እንዳለባቸዉ ገልጸዋል።
በመጠቃለያ ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ እና ክቡራን ሚኒስትር ዴኤታዎች ከተሳታፊዎች ጋር ዉይይት ተደርጓል። በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነ መድረክ በትራንስፖርት ዘርፍ በመዘጋጀቱና ባለሀብቱን ለማሳተፍ መንግስት ቁርጠኝነቱን ማሳየቱን አድንቀዉ በዘርፉ ስላሉ የኢንቨስትመንት ዕድሎች ላይ በተሰጣቸዉ ማብራርያ መደሰታቸዉን ገልጸዉ በትራንስፖርት ኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ ግልጽነት የሚሹ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች አንስተዉ ምላሽና ማብራርያ በክብርት ሚኒስትርና በክቡራን ሚኒስትር ዴኤታዎች ተሰጥቷል።
በመጨረሻም ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ የጉባኤዉ ተሳታፊዎችን አመስግነዉ በትራንስፖርት ዘርፉ ለግሉ ባለሀብት በመንግስት በተመቻቸዉ ዕድሎች እንዲጠቀሙ በቅርበት እንደሚሰሩና ለስኬቱ አሰፈላጊዉን አደረጃጀቶችና አሰራሮችን በመዘርጋት እስከመጨረሻዉ በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸዉን አረጋግጠዋል።

የዜና ክምችት የዜና ክምችት