የተጀመረው ሀገር አቀፍ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ንቅናቄ ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡

"ከጳጉሜን እስከ ጳጉሜን #እንደርሳለን!" በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ሀገር አቀፍ የመንገድ ትራፊክ ደህንነት ንቅናቄ በአዲሱ አመትም ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
በአዲሱ አመት ዋዜማ የጳጉሜን 5ቱን ቀናቶች በተለያዩ መርሀ-ግብሮች ሲካሄድ የቆየው ሀገር አቀፍ ንቅናቄ በህብረተሰቡ ያላቀ ተሳትፎ ማሳካት ተችሏል፡፡ እንደሚታወቀው የትራንስፖርት ሚኒስቴር #ጳጉሜን_1 የሳይክል እና የእግረኞች ቀን፣ #ጳጉሜን_2 የትራፊክ አደጋን ለመከላከል የእግር ጉዞ እነዲሁም ከብዙሃን ማህበራት ጋር የተዘጋጀ የምክክር መርሃ ግብር፣ #ጳጉሜን_3 የቁጥጥር ቀን ‹‹የቁጥጥር ሥርዓቱን በማዘመን በትራፊክ አደጋ የሚደረሰውን ጉዳት በጋራ እንከላከል።›› #ጳጉሜን_4 “የሚዲያዎች ሚና በመንገድ ደህንነት_ዙሪያ›› እንዲሁም #ጳጉሜን_5 የፍጥነት ገደብን የማክበር ቀን ‹‹መልካም ዜጋ የፍጥነት ወሰንን አያልፍም›› የሚሉ መልእክቶችን መሰረት በማድረግ እየከፋ የመጣውን የመንገድ ትራፊክ አደጋ ለመከላከልና ለመቀነስ የሚያስችል ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ማከናወን ተችላል፡፡
በንቅናቄው ዘመቻ በአንድ በኩል ሚኒስቴር መስሪያ ቤታችን ባከናወናቸው የፓናል ውይይቶችና ልዩ ልዩ መርሃ-ግብሮች ከህብረተሰቡና ከባለድርሻ አካላት ግብአት መሰብሰብ የቻለበት በሌላ በኩል ለአደጋ መንስዔ ተብለው የተለዩ ምክንያቶችን ህብረተሰቡ ግንዛቤ እንዲጨበጥ እና የመከላከል ስራው ላይ ዋንኛ ተዋናያን እንዲሆን የሚያስችል ወጤት ተገኝቷል፡፡
መንግስት የዜጎችን ደህንነት የማረጋገጥ ሃላፊነትና ግዴታ እንዳለበት ይታመናል በመሆኑም የመንገድ ትራፊክ ደህንነት የአንድ ሰሞን ተግባር ብቻ ሳይሆን ተከታታይና ወጥ ስራ ይጠይቃል ለዚህም "ከጳጉሜ እስከ ጳጉሜ #እንደርሳለን!" ብለን የጀመርነው ሀገር አቀፍ ንቅናቄ በመጪው አዲስ አመትም አጠናክሮ በማስቀጠል ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ከአስከፊው የመንገድ ትራፊክ አደጋ ለመታደግ ከመላው ህዝባችን ጋር በመቀናጀት ለለውጥ እንሰራለን፡፡
"ከጳጉሜን እስከ ጳጉሜን #እንደርሳለን!"
መልካም አዲስ አመት !!
 

የዜና ክምችት የዜና ክምችት