የትራንስፖርት ሚኒስቴር የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ የአፈጻጸም ሪፖርት ላይ ዉይይት ተደረገ፡፡

የትራንስፖርት ሚኒስቴር የአገልግሎት አሰጣጥ ማሻሻያ ካዉንስል ከጥር/2012 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ መልክ ተደራጅቶ በሚኒስቴር መ/ቤቱና በተጠሪ ተቋማት የክትትልና ድጋፍ ሥራ መጀመሩ ይታወሳል ፡፡
በዛሬዉ ዕለት በተጀመረዉ የክትትልና ድጋፍ ሥራ ላይ በዋናናት በዚህ በጀት ዓመት የተከናወኑ ክንዉኖችንና በወቅታዊዉ የኮሮና ባይረስ ስርጭትን ከመከላከል አንፃር እየተሠሩ ያለዉን ሥራ ትኩረት በማድረግ ካዉንስሉ ባዘጋጀዉ ቼክ ሊስት መሠረት ወደ እያንዳንዱ ተቋማት በአካል በመገኘት ከአገልግሎት አሰጣጥ ጋር ያለዉን ጥንካሬና ድክመት በመገምገም በሚሻሻልበት ሁኔታ ላይ ስምምነት ላይ በመድረስ የማጠቃለያ ሪፖርቱን ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ እና ክቡራን ሚኒስትር ዴኤታዎች በተገኙበት ቀርቦ ወይይት ተደርጓል፡፡
የካዉንስሉ ሰብሳቢ ኢንጅነር ፀደቀ ዘዉዴ ስለ ገምገማዉ ዓላማ ሲናገሩ ሚኒስቴር መ/ቤቱና ተጠሪ ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ዘመናዊና በተቀመጠው ስታንዳርድ መሠረት ህብረተሰቡን የሚያረካ ስለመሆኑና ቅሬታዎችም ከመፍታት አንፃር ያለበትን ደረጃና ዝግጁነት በመገምገም በቀጣይ የተሻለ የአገልግሎት አሰጣጥ በትራንስፖርት ዘርፉ እንዲሰፍን በጋራ መስራት ነዉ ብለዋል፡፡ እንደ ትራንስፖርት ዘርፍ በቺክሊስቱ መሠረት ለሚኒስቴር መ/ቤቱ ተጠሪ የሆኑ ተቋማትን የአገልግሎት አሰጣጥ በተቀመጠዉ ስታንዳርድ መሠረት ስለመሆኑ በመገምገም የካዉንስሉ አባላት የዘርፉን ጠንካራና ደካማ ጎኖችን በመለየት በሪፖርቱ በዝርዝር አቅርበዋል።
ከክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስና ከክቡራን ሚኒስትር ዴኤታዎች ጋር በተደረገው የማጠቃለያ የምክክር መድረክ የትራንስፖርት ዘርፉ የአገልግሎት አሰጣጥ በሚሻሻልበት ሁኔታ ላይ ሰፊ ዉይይትና የጋር አቅጣጫ ማስቀመጥ ተችሏል። ክብርት ሚኒስትር ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ በሪፖርቱ በጠንካሬና በድክመት የተነሱትን ሚኒስቴር መ/ቤቱ በግብዓትነት እንደሚጠቀመውና በቀጣይ ዕቅዶችም ተካተዉ የተገልጋዩን ህብረተሰብ እርካታ ለማሳደግ እንደሚሠራ አንስተዋል።

የዜና ክምችት የዜና ክምችት