የኢፌዴሪ የትራንስፖርት ሚኒስቴር በዚህ ክረምት ለሚከናወነዉ የችግኝ ተከላ መረሃ ግብር የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማጠናቀቁን ገለፀ።

የሚኒስቴር መ/ቤቱ የአከባቢና የአየር ንብረት ለዉጥ ዳይሬክቶሬትና ሌሎች ባለሙያዎች ዛሬ በአዲስ አዳማ ፈጣን መንገድ ላይ በሞጆ አከባቢና በምስራቅ ሸዋ ዞን ሎሚ ወረዳ ኦርባ-ጎዴ ቀበሌ ባለፈዉ አመት የተተከሉ ችግኞች ያሉበትን ሁኔታ ለማየት የተቻለ ሲሆን ሁሉም ችግኞች በጥሩ ደረጃ ላይ እንደሚገኙና ከተተከለዉም 85% መጽደቁን የአከባቢና የአየር ንብረት ለዉጥ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጆቢር አየሌዉ ገልፀዋል።
ከቦታ ልየታ አንፃርም የችግኝ ተከላዉ የሚከናወነዉ በሀገሪቱ እየተሰሩ ባሉት የመንገድና ባቡር ፕሮጀክቶች ዙሪያ፣ በፈጠን መንገዶች (በአዲስ-አዳማ እና ድሬዳዋ-ደወሌ ፈጣን መንገድ) እና በዙሪያዉ ባሉት ወረዳዎች መሆኑ ታውቋል። በመሆኑም የጉድጓድ ቁፋሮ ስራዎች በስፋት እየተሰሩ ስለመሆናቸዉ በአካል በባለሙያዎቹ የታየ ሲሆን በቅርቡም የተከላ ስራ እንደምጀመር ለማወቅ ተችሏል።
ተገቢዉን ጥንቃቄ በማድረግና ከንክኪ ዉጪ በሆነ መልኩ አካላዊ ርቀትን በመጠበቅ የተከላ ሥራን በማከናወን የኪቪድ-19 ስርጭትን እየተከላከልን ባለፈዉ አመት የተገኘዉን ሀገራዊ ድል ዘንድሮም ለመድገም እንደሚሠራ ተገልጿል።

የዜና ክምችት የዜና ክምችት