ማስታወቂያ ለድንበር ተሻጋሪ እና የሀገር ውስጥ የደረቅ ጭነት ትራንስፖርተሮች እና ድርጅቶች በሙሉ

የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ከሚያዚያ 26 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በ 60 ቀናት ውስጥ የአፈር ማዳበሪያ እና ስንዴ ወደ ሀገር ውስጥ ሙሉ በሙሉ አጓጉዞ ለመጨረስ ውል በገቡት ትራንስፖርተሮች አቅም ብቻ መፈጸም ስለማይቻል ተጨማሪ ትራንስፖርተሮችን ማሰማራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በድንበር ተሸጋሪ እና በአገር ውስጥ የተደራጃችሁ የደረቅ ጭነት ትራንስፖርት ማህበራት እና ድርጅቶች የኮታ ድልድል የተሰጣችሁ በመሆኑ የተዘጋጀላችሁን ደብዳቤ በፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ቢሮ ቁጥር 204 በመምጣት እንድትወስዱ እየገለጽን ከሚያዚያ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ በኮታችሁ መሰረት ወደ ወደብ ተሽከርካሪዎቻችሁን በመላክ ሀገራዊ ሀላፊነታችሁን እንድትወጡ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡
የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን

የዜና ክምችት የዜና ክምችት