አገር አቋራጭ የትራንስፖርት አገልግሎት በፈረቃ መሆኑ ኮሮናን ለመከላከል ፋይዳው የጎላ ነው ሲሉ ተገልጋዮችና የትራንስፖርት ማህበራት ገለጹ

አገር አቋራጭ የትራንስፖርት አገልግሎት በፈረቃ መሆኑ ኮሮናን ለመከላከል ፋይዳው የጎላ ነው ሲሉ ተገልጋዮችና የትራንስፖርት ማህበራት ገለጹ
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስፈጸም በወጣዉ ድንጋጌ የሚኒስትሮች ኮሚቴ የትራንስፖርት ዘርፍ አፈፃጸም መመሪያ አውጥቶ ወደ ስራ መግባቱ ይታወሳል።
ይህም አሰራር የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል እና አካላዊ ርቀት ለመጠበቅ ከአዲስ አበባ ወደ ተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች የሚጓዙ የሀገር አቋራጭ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪዎች በፈረቃ እየተስተናገደ እንደሆነ የፌዴራል የትራንስፖርት ባለስዕልጣን ገልጿል።
ምንም እንኳን የፈረቃ አሰራሩ በዓል ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በአገልግሎት ላይ የተወሰነ መጨናነቅ ቢፈጥርም ኮሮና እንዳይተላለፍ ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑን ነው ተገልጋዮችና የትራንስፖርት ማህበራት የገለጹት።
በዚህም በህግ ከተፈቀደላቸዉ የሠው ብዛት 50 በመቶ ብቻ እንዲጭኑ መወሰኑ እና በፈረቃ መሆኑ ችግሩ እንዳይባባስ እንደሚያደርገውም ጠቁመዋል።
በተመሳሳይ በመመሪያው ላይ የሀገር አቋራጭ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎቶችን ሲሰጡ የሚያስከፍለትን የታሪፍ ጭማሪ በተመለከተ ከመደበኛ ዋጋው 50 ከመቶ ጭማሪ ያለው መሆኑን ተነግሯል።

የዜና ክምችት የዜና ክምችት