የሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የታሪፍ ጭማሪን በተመለከተ።

የሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የታሪፍ ጭማሪን በተመለከተ።
**********
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን ለማስፈጸም በወጣዉ በሚኒስትሮች ም/ቤት በተሰየመዉ የሚኒስትሮች ኮሚቴ የትራንስፖርት ዘርፍ አፈፃጸም መመሪያ መሰረት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል እና አካላዊ እርቀት ለመጠበቅ ከአዲስ አበባ ወደ ተለያዩ የሀገሪቷ ክፍሎች የሚጓዙ የሀገር አቋራጭ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪዎች በህግ ከተፈቀደላቸዉ የሠው ብዛት 50% ብቻ እንደሚጭኑ መወሰኑ ይታወቃል፡፡
በተመሳሳይ በመመሪያው ላይ የሀገር አቋራጭ የህዝብ ማመላለሻ ተሸከርካሪዎች የትራንስፖርት አገልግሎቶችን ሲሰጡ የሚያስከፍለትን የታሪፍ ጭማሪ በተመለከተ ከመደበኛ ዋጋው 50 ከመቶ ጭማሪ እንደሚኖረው በግልጽ የተቀመጠ ከመሆኑም በላይ ዝርዝሩ በባስልጣኑ እንደሚወሰን ተደንግጓል።
በመሆኑም በመመሪያው መሠረት በፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የተወሰነውን ዝርዝር የታሪፍ ማሻሻያ እንደሚከተለው ያቀረብን ስለሆነ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መሠረት ለተግባራዊነቱ ሁሉም እንዲተባበር እንጠይቃለን።

የዜና ክምችት የዜና ክምችት