የኢፌዴሪ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ አወል ወግሪስ ከክሬዲት ሱዊዝ ባንክ አመራር አካላት ጋር ተወያዩ፡፡

የአፈር ማዳበሪያ የጫነች የመጀመሪያዋ መርከብ ጅቡቲ ወደብ ደርሳለች

የኢፌዴሪ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ አወል ወግሪስ ከክሬዲት ሱዊዝ ባንክ አመራር አካላት ጋር ተወያዩ፡፡
**************************************************************************************
ክቡር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አወል ወግሪስ ከዴንማርክና ሲዊዘርላንድ ከመጡ ልዑካን ጋር የተወያዩት በዋናነት የአዋሽ-ወልዲያ-ሀራ ገበያ ፕሮጀክት አጠቃላይ የአፈፃፀም ሂደትና በፕሮጀክቱ ላይ ስለሚሠራዉ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ታዉቋል፡፡ ከልዑካን ቡዱን ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ከሚኒስቴር መ/ቤቱ ከፍተኛ ባለሙያዎችና ከክቡር ሚኒስትር ዴኤታ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል፡፡ በተለይም የፕሮጀክቱን የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታን በተመለከተ ጨረታ ወጥቶ የፋይናንሻልና የቴክኒካል ግምገማ በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ክትትል እየተደረገ ስለመሆኑ ለልዑካኑ ተገልፆላቸዋል፡፡ ከክሬዲት ሱዊዝ ባንክ የመጡ ከፍተኛ የአመራር አካላትም በፕሮጀክቱ ለሚከናወነዉ የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ መንግስት ስለወሰደዉ የመፍትሔ እርምጃ አመስግነዋል፡፡ ክሬዲት ሱዊዝ ባንክ ለአዋሽ-ወልዲያ-ሀራ ገበያ ፕሮጀክት ክንዉን ብድር የሰጠ ባንክ መሆኑ ይታወቃል፡፡


የዜና ክምችት የዜና ክምችት